አምቦ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ባደረገው ጥሪ መሰረት ከዛሬ ጥቅምት 17/2018 ዓ/ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው 2 ካምፓሶች ማለትም በዋና ካምፓስ እና በሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደቡ ከ2 ሺህ በላይ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል፡፡
በአቀባበል ሂደቱ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ኅብረት ተማሪዎችን ከአምቦ መናኸሪያ ከመቀበል ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉላቸው ይገኛሉ፡፡