የአምቦ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም መሪ ዕቅድ የካውንስል ውይይት፤መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም

አምቦ ዩኒቨርሲቲ በ2018 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ለይ ከዩኒቨርሲቲዉ ካውንስል ጋር ዛሬ ውይይት አደረገ፡፡ ለውይይቱ መነሻ በ2017 በጀት ዓመት በትኩረት መስኮች እና ቁልፍ ተግባራት መሠረት የተሰሩ ስራዎች ላይ፤ በገጠሙት ችግሮች፤ ደካማ ጎኖች እና ጠንካራ ጎኖች ላይ በዕቅድ እና በጀት ዲይሬክቶሬት አጠቃላይ ገለፃ ከተደረገ በኋላ ከካውንስል አባላት ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ባይሳ ለታ ሰፊውን የዩኒቨርሰቲ ስራን የሚያስተባብር እንዲሁም ሰርቶ የሚያሰራ ካውንስሉ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተባብሮ፣ተቀናጅቶና ተጋግዞ በመስራት እያንዳንዱ የሥራ ክፍል ስራዎችን በዕቅድ እንዲሰሩ ከዚያ በላይም ለውጤቱ እንዲተጉ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልፀዋል፡፡ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ፕ/ር ብዙነሽ ሚደክሳም የተነሱ ሃሳቦችን እንደ ግብዓት ወስደን የካውንስሉ አባላት ለእያንዳንዱ ሠራተኛ ዕቅዱ ግልፅ እንዲሆን መስራት አለበት በማለት መልእክት አስተላልፏል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የካውንስል አባላትም ስራዎችን ተቀናጅተው ለመስራት እንዲሁም የተገኘውን ውጤት የጋራ ለማድረግ መሰል ውይይቶች አስፈላጊ እንደሆነ አስተያየት ሰተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *