አምቦ ዩኒቨርሲቲ በአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ለተመደቡ ተማሪዎች ቅበላ አደረገ

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደዉ፣ በአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ፕሮግራም 4975 ተማሪዎች በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል፡፡ ከተመደቡት 4975 ተማሪዎች መካከል 2835 የተፈጥሮ ሳይንስ ሲሆኑ 2140 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸዉ። ለተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲዉ ከመጋቢት 07-08/2015 ዓ.ም እንዲገቡ ባደረገላቸዉ ጥሪ መሰረት በዛሬው ዕለት ማለትም በ07/07/2015 ዩኒቨርሲቲዉ እነዚህን ተማሪዎች መቀበል የጀመረ ሲሆን፤ ቅበላው በነገው ዕለትም ይቀጥላል፡፡
ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ አምቦ ዩኒቨርሲቲ በደህና መጣችሁ፤ መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንላችሁ !!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *